ብዙዎቻችን ለጸሎትጊዜ እንደማይተርፈንእንናገራለን፡፡ ነገር ግንከኛ በላይ በኃላፊነትእና በሥራ ይጣደፉየነበሩ ሰዎች ለጸሎትጊዜ እንደነበራቸውስናይ እኛ ጊዜ ሳይሆንፍላጎት እንደሌለንእንገነዘባለን፡፡
በዘመነ መሳፍንትተበታትና የነበረቺውንኢትዮጵያ አንድለማድረግ ያለ ዕረፍትላይ ከታች ይኳትኑየነበሩት ዐፄ ቴዎድሮስምንም እንኳን ፋታባይኖራቸው ለጸሎት ግን ጊዜ ነበራቸው፡፡
ንጉሥ ቴዎድሮስ ለጸሎት ማልደው መነሣት ልማዳቸው ነበር፡፡ ከመኝታ እልፍኛቸውወጥተው ጋቢያቸውን ይከናነቡና ድንጋይ ላይ ቁጭ ብለው ጸሎታቸውን ያደርሳሉ፡፡ አቡነዘበሰማያት፣ የዕለት ውዳሴ ማርያም እና መልክዐ መድኃኔዓለም የዘወትር ጸሎቶቻቸውነበሩ፡፡ ጊዜ ካገኙም ዳዊት ይደግሙ ነበር፡፡
TewodrosIIIIIIIIIII
TewodrosIIIIIIIIIII

